#በወቅታዊ_ሀገራዊ_ጉዳዮች_ላይ_ውይይት_መድረክ_ተካሄደ!!!
*******************************************************
ዛሬ ግንቦት 05/2014 ዓ.ም: የኮሌጃችን አሰልጣኝ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ያሳተፈና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
በውይይቱ መጀመሪያ ላይ የኮሌጃችን ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን ለውይይቱ መነሻ እንዲሆን የተዘጋጀውን ሰነድ በተብራራና ግልጽ በሆነ ሁኔታ አቅርበዋል። በሰነዱም እንደተመላከተው ሀገራችን ለተያያዘችው ለውጥ መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮቶች ያሉት መሆኑን፤ እነዚህንም መልካም አጋጣሚዎች ለመጠቀምና ተግዳሮቶችን ለመሻገር የሚቻለው የመንግስትና የህዝቡ ተባብሮ መስራት ሲችሉ መሆኑን እና የእያንዳንዱ ተግዳሮት ማሰሪያ ደግሞ የሰላምና ፀጥታን ማረጋገጥ ሲቻል መሆኑን በዝርዝር ቀርቧል።
ሰነዱ ከቀረበ በኋላ የውይይቱ ተሳታፊዎች አስተያየትና ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን የቀረበው ሰነድ በትክክል ወቅታዊ ሀገራዊ ችግራችንን ፍንትው አድርጎ ያሳየ መሆኑን በጠንካራ ጎን ያነሱ ሲሆን መሰል ውይይቶችም በተከታታይነት ቢካሄዱ የህዝቡን የልብ ትርታ ከማወቅ በተጨማሪ የዴሞክራሲ ስርዓቱን በማዳበር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አንስተዋል፤ ከዚህ በተጨማሪ የሀገርን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ ተግባርና ኋላፊነት እንደሆነ አንስተዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በተለያዩ ዘርፎች እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች ዙሪያ ከተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎች አንስተዋል፤ የመድረኩ መሪዎች የተነሱ ጥያቄዎችን በየደረጃው ለሚመለከታቸው አካላት እንደሚያቀርቡ ገልፀዋል። በአጠቃላይ ልማትን በማፋጠን፣ መልካም አስተዳደር በማስፈን፣ ሰላምና ፀጥታ ማረጋገጥ፣ የኑሮ ውድነትን መቆጣጠር የመሣሠሉት ጉዳዮች የክፍተት ምንጭ የሆኑ ከበላይ እስከ ታችኛው መዋቅር የሚገኙ አመራሮች ጀምሮ በተገቢው ራሳቸውን ማየት እንዳለባቸውና የቁጥጥር ስርዓቱ ጠንካራ መሆን እንዳለበት በሰፊው አንስተዋል።
0 Comments
10 Q