#የተማሪዎች_ጉብኝት!!!

**********************
የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ዩኒቨርስቲ እና የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት በመተባበር በወልቂጤ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ት/ቤቶች ስር በተቋቋሙ የሳይንስና ፈጠራ ክበባት ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ለባለተሰጥኦ ተማሪዎችና ለት/ት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ የሒሳብና ኢንጅነሪንግ ላይ ግንዛቤ የሚፈጥር የጉብኝት መርሐ-ግብር በኮሌጃችን ተካሂዷል።
በጉብኝቱ ላይ የኮሌጁ ዲኖች፣ የት/ት ክፍሎች ኃላፊዎች ተገኝተው ሰፊ ገለፃ አድርገዋል። የጉብኝቱ ተሳታፊዎችም ጥያቄዎች በማቅረብ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፤ መሠል ጉብኝቶች መዘጋጀታቸው የሳይንስ፥ የቴክኖሎጂ፥ የሒሳብና ኢንጅነሪንግ ላይ ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ ለሀገር እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው እንዲሁም የፈጠራ ችሎታና ያላቸው ተማሪዎች ከስር ጀምሮ ችሎታቸው እንዲያድና እንዲዳብር ከማድረጉም በተጨማሪ በህብረተሰቡ ዘንድ ስለቴክኒክና ሙያ ያለውን የተዛባ አመለካከት በማስተካከል በኩል የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል።