********************************************************
ዛሬ ታህሳስ 16/2014 ዓ.ም: የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ዩኒቨርሲቲ በዲግሪና በደረጃ ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች በደማቅ ፕሮግራም አስመርቋል። ለምርቃት የበቁት በቀን፣ በማታና በሳምንቱ መጨረሻ የሰለጠኑ ሲሆን በዲግሪ መርሐ-ግብር 31 ሰልጣኞች እንዲሁም ከደረጃ 2-5 921 በድምሩ 952 ናቸው። በፕሮግራሙ ላይ የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ እና የኮሌጁ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ እንዳለ ገ/መስቀል እና የካቢኔ አባላት፣ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/የቴ/ሙ/ት/ሥ/ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር እንዳልካቸው ጌታቸው እና ም/ቢሮ ኃላፊዎች እና የጉራጌ ዞን የቴ/ሙ/ት/ሥ/መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈቱ አብዶን፣ የኮሌጁ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን ጨምሮ የክልሉ የብቃት ምዘና ማረጋገጫ እና የቴ/ሙ/ት/ሥ/ኤጀንሲዎች ዳይሬክተሮች፣ የኮሌጁ የቦርድ አባላት፣ የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆችና በዞኑ የሚገኙ ኮሌጆች ዲኖች፣ የኮሌጁ የማኔጅመንት አባላትና መምህራን ሰራተኞች፣ የተመራቂ ሰልጣኝ ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በተጨማሪም የተገኙ እንግዶች የተለያዩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቶች እና የስራ መመሪያ አስተላለፋቸው በተጨማሪ የጋርመንት ት/ት ክፍል ተመራቂ ሰልጣኞችና አሰልጣኝ መምህራን ደስ የሚል የፋሽን ሾው ፕሮግራም አዘጋጅተው የፕሮግራሙን ተሳታፊዎች አዝናንተዋል።
0 Comments
10 Q