#ዓመታዊ_የፀረሙስና_የፀረ-ኤድስና_የነጭ_ሪቫን_ቀን_በዓላት_ተከብረዋል።

**************************************
ህዳር 24/2014 ዓ.ም: የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞችና አስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት የ2014 ዓ.ም የፀረሙስና፣ የፀረ-ኤድስ እና የነጭ ሪቫን ቀን በዓላት በጋራ ተከብረዋል።
የበአሉን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን 3ቱንም በዓላት የምናከብረው ለአላማና ግንዛቤ ተወስዶ ለመተግበር መሆኑንና ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ በንቃትና በትኩረት በዓላቱን እንዲያከብ አፅንኦት ሰጥተው በመግለፅ ፕሮግራሙን አስጀምረዋል።
በዚህም መሰረት "በሥነምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያ!!!" በሚል መሪ ቃል በሀገር ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ የተከበረውን አለምአቀፍ የፀረሙስና ቀን በክልል ደረጃ ተዘጋጅቶ በወረደ የውይይት ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ሲሆን ተሳታፊዎችም ካነሷቸው አስተያየቶች መካከል አሁን ሀገራችን ተገዳ የገባችበት የህልውና ጦርነት መነሻ የስግብግቡ ጁንታ ራስ ወዳድ የስነምግባርና የሙስና የመዘፈቅ ችግር መሆኑን፤ ሙስና የመልካም አስተዳደር ችግር እንደሚፈጥር፤ ሙስና በዴሞክራሲያዊ፣ንና ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳቶቹ ሰፊ ስለመሆናቸው ተነስቷል።
በሌላ በኩል የተከበረው የፀረ-ኤድስ ቀን ሲከበር ያለ ጤንነት የሀገርን ልማትና ብልጽግና ማረጋገጥ እንደማይቻል ሁሉም ማህበረሰብ ሊረዳው እንደሚገባና በተለይም የኤድስ በሽታን 3ቱን #መዎች በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ ወረርሽኙን መግታት እንዳለብንና የዜግነት ግዴታችንን መወጣት እንዳለብን በአፅንኦት ተሰጥቶበታል።
እንዲሁም የአለም አቀፍ የነጭ ሪቫን ቀንም ሲከበር በሀገራችን በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ያለውን ፆታዊ ጥቃት እንዲቆም ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለ ተነስቷል።
በአጠቃላይ የበዓላቱ አከባበር ከወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ጋርም በማገናኘት ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ የጭቆና ቀንበርን መልሶ ለማምጣት ሀገራችንን በመውጋት ላይ ያለውን ስግብግብ ጁንታ ለመጀምሰስ ለሚደረገው የህልውና ዘመቻ ሁሉም የበኩሉን ለማበርከት ቃል የገባበትም ጭምር ነበር።