በጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ስር የሚገኙ 11 የመንግስት ኮሌጆች በዛሬው ዕለት ማለትም በቀን 22/03/2014 ዓ/ም የሁሉም ኮሌጆች ዋና ዲኖችና የመምሪያው የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ከክልል የወረደውን የሀገራዊ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ዕቅድን መነሻ በማድረግ የተቋማቱን የ4 ወር ከ15 ቀን ዕቅድ አፈፃፀም ያለበት ደረጃን በሰፊው የተገመገመ ሲሆን በኮሌጆቹ በኩል የታዩ ጠንካራ ተግባራትን እና በቀጣይ መሻሻል ያለባቸውን ነጥቦች አጉልቶ በማሳየት የአፈፃፀም ደረጃቸው የወረዱ ተቋማት ለቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማድረግ አጽንኦት ሰጥተው እንዲሰሩ በመምሪያው ኃላፊ በአቶ ፈቱ አብዶ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በመቀጠልም የውይይቱ ተሳታፊዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደጀን ለመሆን በሚያስችል መልኩ በየኮሌጆቻቸው ከሚገኙ አሰልጣኞች፣የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም ከሰልጣኞች ጋር የጋራ ውይይት አድርገው በተለያዩ ኩነቶች ላይ እየተሳተፉ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን
1. ከሁሉም ኮሌጆችና የመምሪያው ሰራተኞች ለሁለት ዙር ያህል ከወር ደመወዛቸው ከ20 እስከ 30 ፐርሰንት ተቀናሽ በማድረግ 865634 ብር ድጋፍ የተደረገ መሆኑ፤
2. ለመከላከያ ሰራዊት የስንቅ ዝግጅትን በተመለከተ በወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እስከ 460000 ሺ ብር ስንቅ መዘጋጀቱ፤
3. በመምሪያው ስር በሚገኙ ሁሉም ኮሌጆች እስካሁን 162 ዩኒት ደም የተለገሰ መሆኑ፤
4. ለወልቂጤ ከተማ ህዝባዊ ሰራዊት የደንብ ልብስ በቁጥር 200 ያህል በገንዘብ ሲተመን 50000 ብር ያህል ድጋፍ የተደረገ መሆኑ፤
5. ለተለያዩ በጎ አድራጎት ስራዎች ማለትም ለቤት ጥገና፣ለትምህርት ቁሳቁስ እና የአልባሳት ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን 795580 ብር ድጋፍ የተደረገ መሆኑ፤
6. በመምሪያው ስር በሚገኙ ሁሉም ኮሌጆች የበሬ፣የበግና የፍየል ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን 105000 ብር የተለገሰ መሆኑና
እንደአጠቃላይ እስካሁን በመምሪያውና በመምሪያው ስር በሚገኙ ኮሌጆች 1816214 ብር በመለገስ በመለገስ ለመከላከያ ሰራዊት ደጀንነቱን በተግባር ያሳየ መምሪያ መሆኑ ተገልፆ ለቀጣይም የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ በማዋቀር ለዘማች ቤተሰብ ሰብል ለማሰባሰብና ተጨማሪ ድጋፎችን ለማድረግ ቃል በመግባት #NO MORE TPLF በሚል ውይይቱ ተጠናቋል፡፡