1 / 7
2 / 7
3 / 7
4 / 7
5 / 7
6 / 7
7 / 7
7 / 7
4 / 7
5 / 7
6 / 7
7 / 7

SNNPRS TVET Bureau በደቡብ ክልል የሚገኙ የግል የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ህግና ስርዓትን ተከትለው መስራት እንዳለባቸው የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ኃላፊ እንዳልካቸው ጌታቸው (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

SNNPRS TVET Bureau በደቡብ ክልል የሚገኙ የግል የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ህግና ስርዓትን ተከትለው መስራት እንዳለባቸው የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ኃላፊ እንዳልካቸው ጌታቸው (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

 


በደቡብ ክልል የሚገኙ የግል የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ህግና ስርዓትን ተከትለው መስራት እንዳለባቸው የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ኃላፊ እንዳልካቸው ጌታቸው (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
============================================
የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ እንዳልካቸው ጌታቸው (ዶ/ር) የግል ኮሌጆች ከድብብቆሽ አሰራር ወጥተው ህግና ስርዓትን ተከትለው መስራት እንዳለባቸውና ይህንን ባላደረጉ የግል ኮሌጆች ላይ ቢሮው ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል፡፡
ከነችግሩም ቢሆን የሰልጣኝ መረጃ በማያስተላልፉ ፣ ሰልጣኞችን ከወቅቱ መቁረጫ ነጥብ በታች የተቀበሉ ኮሌጆችን ፣ ከተፈቀደላቸው ፈቃድ ውጪ ስልጠና በሚሰጡ ኮሌጆች ፣ ባልተመዘኑና ተገቢውን አሰልጣኞች በማይቀጥሩ ኮሌጆች ላይ ህግና ስርዓቱን ተከትለው ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስዱ እንዳልካቸው ጌታቸው (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ለማንኛውም የቴክኒክና ሙያ ፈቃድ መስጠት ማቆማቸውንና ከዚህ በኃላ የዞኑ መንግስት በራሱ ካቢኔ ውሳኔ መሰረት ለዚህ አከባቢ ይህ ሙያ ይፈቀድልኝ የሚል ጥያቄ ከቀረበ ፈቃድ እንደሚሰጥ የገለጹት እንዳልካቸው ጌታቸው (ዶ/ር) የዞኑ ቴክኒክና ሙያ መምሪያ በሚሰጠው የድጋፍ ደብዳቤ መሰረት ፈቃድ እንደማይሰጥ ተናግረዋል፡፡
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ መንግስት ብቻውን ሁሉንም የልማት ዘርፎች ተሸክሞ መሄድ ስለማይችል የግሉ ዘርፍ ከመንግስት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት እንዳለበትና ይህንን ዕድል በማይጠቀሙና በወረደ አስተሳሰብ ትውልድን ለማበላሸት በሚጠሩ ኮሌጅች ላይ በህዝብ ጉዳ መደራደር ስለማይቻል ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድባቸው ገልጸዋል፡፡
የደቡብ ክልል ቴክኒክ ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አጥና አስፋው የትኛውም ኮሌጅ ሰልጣኞችን ከመቁረጫ ነጥብ በታች መቀበል እነደሌለበት ፣የፕሮግራም ምዘገባ ፈቃዳቸውን ለተገልጋይ በሚታዩ ቦታዎች ላይ መስቀል እንዳለባቸውና በተሰጣቸው ፈቃድ ብቻ ስልጠና መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የደቡብ ክልል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሚልከያስ ካልሳ እንደ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲም ህገ ወጥነትን ለመከላከል የተለያዩ ስራዎችን መስራት መቻላቸውንና ህግና ስርዓትን ተከትለው በማይሰሩ የግል ኮሌጆችን የምዘና አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረግ መቻላቸውን ፣ የተወሰኑ ኮሌጆችን ደረጃ ዝቅ የማድረግ ስራ መስራት መቻሉን ገልጸዋል፡፡
የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስትቲዩት የቴክኖሎጂ ምርምር ና ልማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገለቱ ገናሞ የመረጃ ግልጸኝነት ያለመኖር ፣የሰልጣኝ መረጃ ለማሳየት ፈቃደኛ ያለመሆን ችግር ፣ የሰልጣኝ መረጃ ለቢሮው ያለመላክ ችግር ፣ ባልበቁ አሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ፣በምዘና የማብቃት ስራ የመጨረሻ ውጤት አድርጎ መውሰድ ና ከሰልጣኝ ቁጥር ጋር በማይጣጣም ላቭ ስልጠና መስጠት ዋና ዋና የኮሌጆቹ ክፍተቶች መሆናቸውን የኢንስፔክስን ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት ገልጸዋል፡፡
ዘገባው የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡





Post a Comment

0 Comments