በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስርፀት ዘርፍ ስር በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ የተሰጠው ሥልጠና የባለሙያዎችን የግንዛቤ ክፍተት የሞላ ነው ተባለ፡፡
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስርፀት ዘርፍ ስር በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ በጨረራ ማሳወቅና ፍቃድ አሰጣጥ፣በአዕምሯዊ ንብረት (ፓተንት ጥበቃ)፣
በሳይንስና ቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ እና በምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር በሚሉ ርዕሶች ላይ ከዞንና ልዩ ወረዳ ለተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ከህዳር 22-23/2014 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት በጌዲኦ ዞን በዲላ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና የባለሙያዎችን የግንዛቤ ክፍተት የሞላ ነው ተባለ፡፡
የሥልጠናውን ዋና ዓላማው የገለፁት የቢሮው ም/ኃላፊና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስርፀት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሂዲን ሁሴን ሥልጠናው ከፌደራል እና ከሳ/ኢ/ቴ/ቢሮ በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን የዞንና የልዩ ወረዳ የዘርፉ ባለሙያዎች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና በቀጣይ በተደራጀና ወጥ በሆነ መልኩ መስራት እንዲቻልና የዘርፉ ተግባራት በዕውቀት እንዲመሩ ማድረግ ነው፡፡ ስለሆነም ውጤታማና ችግር ፈቺ የፈጠራና የምርምር ሥራዎችን በመስራትና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ለሀገራዊ ዕድገታችን የበኩላችንን አስተዋፅኦ ማበርከት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
የሥልጠናው ተሳታፊና የጌዲኦ ዞን ሳ/ቴ/ፈ/ሥ/ድ/ክትትል አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አሸናፊ ወንዳፍራሽ በተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ እንዲህ ዓይነት ሥልጠና መሰጠቱ ማን ምንና እንዴት መስራት እንዳለበትና ቀድሞ ይገጥሙን የነበሩ ችግሮችን የምናልፍበትና በቀጣይ በጥሩ አቅም የምንሰራበትን ዕውቀት ያገኘንበት ሥልጠና ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ እንዲሁም የሀዲያ ዞን ሳ/ቴ/ፈ/ሥ/ድ/ክ/ ዳይሬክቶሬት ፈጻሚ የሆኑት አቶ ሊሬ ዋሚሾ ሥልጠናው ከዚህ በፊት በሥራችን ላይ ብዥታ የፈጠሩብንን ነገሮች ያጠራልንና ወቅታዊ በመሆኑ በቀጣይ ሥራችንን በተሳለጠ መልኩ መስራት እንድንችል ተነሳሽነት ፈጥሮብናል በማለት ገልጿል፡፡
በውይይት ወቅትም ሰልጣኞች ላነሷቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ከአሰልጣኞችና ከዘርፉ ኃላፊ ምላሽ የተሰጣቸው ሲሆን በመጨረሻም የቢሮው ም/ኃላፊና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስርፀት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሂዲን ሁሴን በዚህ ዘርፍ የሚሰሩ ማናቸውም ተግባራት የዘርፉን ባለሙያዎችና አመራሮች ስለሚመስል ያለንን ኃይልና ዕውቀት አሟጠን በመጠቀም የተዋጣለት ሥራ ሰርተን ዕቅዳችንን ከግብ ማድረስ ይጠበቅብ ሲሉ አበክረው ማሳሰባቸውን የቢሮው መ/ኮሙኒኬሽን ዘግቧል፡
0 Comments
10 Q